Get Adobe Flash player

መሸሻ የተባለ ክርስቲያን በጊንር ከተማ በእስላምና እምነት ተከታዮች መቃብር ውስጥ ተጥሎ ተገኘ፡፡

 

መሸሻ   አንድ ረቡዕ እለት 12 ሰዓት ላይ ልባሽ ጨርቅ እንዲገዛ ጥሪ ተደረገለት ና ከስራ ቦታው ሄደ፡፡ በጊዜ ወደ ቤቱ ያለመመለሱ ያሳሰበው አብሮት የሚኖረው የአጎቱ ልጅ ሁኔታው  ለ ፓሊስ አመለከተ ፡፡ ፓሊስ ያለመታሰሩን ካስረዳው በሁዋላ ሌላ የርሱን የሚያውቁትን ዘመዶቹና ጓደኞቹን ጨምሮ ፍለጋ እንዲያሰማራ አሳሰቡት ፡፡ በዚህም ሃሙስ እለት ሲፈልገው ውሎ ወደ ዘጠኝ ሰዓተት ላይ የመሸሻን አንድ እግር ጫማ በማግኘቱ ድንጋጤውን ተቆጣጥሮ ወደ ፓሊስ ጣቢያ አመራ ፡፡ የዚህ ወጣት ልጅ ጥርጣሬ እውነተኛ መሆኑን አምነው ፓሊሶች ጫማውን ወደ ተገኘበት ቦታ እንደደረሱ የደም ነጠብጣብ ስላገኙ የነጠብጣቡ መጨረሻ የዚያ አካባቢ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ቀብር ስፍራ ውስጥ አንድ ጉድጉዋድ ውስጥ ቆመ፡፡ ፓሊስም በቆየ መቃብር ላይ አዲስ አፈር ስላገኙ በእርግጠኝነት ሰው መቀበሩን አልተጠራጠሩም፡፡   የሚመለከታቸው ሰዎች በተገኙበት ቁፈራ ለማካሄድ ስለመሸ  ቀብር  ሰፍራው ጥበቃ እንዲደረግ ከሙዋቹ ዘመዶችና ፓሊሶች አዳር ሲጠብቁ አድረው በማግስቱ የሚመለከታቸው ሰዎች ባሉበት ቀብሩ ሲከፈት ወጣት መሸሻ አጁ ወደ ኋላ ታስሮ አንገቱ ተቆጦ ነበር ፡፡ ኢትዮጵያዊያንን የማይመጥን ስለሆነ  ፎቶውንም ሆነ ሙሉ ሰሙን  ማውጣት አልፈለግንም፡፡

ወደ አዲስ አበባ ለአሸራ ምርመራ ተወስዶ ለዘመዶቹ አስክሬኑን እንዲወስዱ ተደርጎ የጊንር ቃለህይወት ቤተክርስቲያን አስክሬኑን  ለቤተሰቦቹ አስረክበው ልባቸው ተሰብሮ ወደ ጊንር ተመልሰዋል፡፡

ገዳዩን ማንነት ና የግድያውን ምንነት ለማጣራት ፓሊስ ክትትል እያደረገ ነው፡፡ የግድያውም ምክንያት ምን እንደሆነ ማጣራት እየተከናወነ ነው፡፡ መሸሻ ለምን ታረደ? ኢትዮጵያዊ  ደመኛውን የሚቀጣበት ወይም  የሚበቀልበት መንገድ እንዳልሆነ ይታወቃል፡፡ የመሸሻ ፓስተር ስለ ህይወቱ ሲናገር እግዚአብሔርን የሚፈራ የጌታን ፊት የሚፈልግ ሁሉንም የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚካፈል ህይወቱ የተለወጠ መሆኑን በሃዘን የገለጸ ሲሆን ይህ ለምን ሆነ ሲል ይጠይቃል፡፡

በእርግጥ ፓሊስ እያጣራው ሲሆን ከደቡብ አካባቢ የመጡትን ክርስቲያኖች ከአካበቢው እንዲወጡ ዘወትር ዛቻ ይከናወን እንደነበር ያነጋገርናቸው ክርስቲያኖች ይገልጻሉ፡፡  ይህን የሃያ ስድስት አመት ወጣት ጌታን መስክሮለት ክትትልና የአገልግሎት ትምህርት አስተምሮት ህይወቱ ወደ አዳኙ ኢየሱስ የሄደ መሆኑ አንድ ነገር ሆኖ ፤ ከርስቲያኖች ና ማንኛውም እምነት ተከታይ የሙዋች ቤተሰቦች መጽናናት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሆንላቸው እንዲጸልዩ እየጠየቅን  ቤተክርስቲያንና መንግስት በየትኛውም ኢትዮጵያዊ  በየትኛውም የእምነት ተከታይ ላይ ፤  ይህን በሰው ዘር ላይ አሰቃቂና አዋራጅ ግድየያ  እንዲያስቆም ኢትዮክርስቲያን ይጠይቃል! ፡፡  

 

 

የዶዶላ መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ወንጌላዊ “የድምጻችን ይሰማ” የሚል ወረቀት በመበተን ተጠርጥሮ ታስሮ ተፈታ

 

አለማየሁ ለገሰ የዶዶላ መጽኃፍ ቅዱስ ተማሪ የነበረው እስልምናን በክርሰትና አተያይ የሚያብራራ ጽሁፍ ፎቶ ኮፒ ሲያደርግ ተገኘ ተብሎ ያለፍርድ ለሶስት ወራት ታስሮ በዋስ የተፈታ ሲሆን ፤ ለአመታት ያህል ፍርድ ቤት በመመላለስ አቃቢ ህግ ምስክር ማቅረብ አቅቶት በመመላለስ ላይ ያለው ሰው  ህዳር 25 ደግሞ አባረው ቤት ሰብረው ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ወንበዴ እንደሚይዝ ሃይል አስጠርተው ቤቱን ከበው፤  በመጨረሻ   ይዘውት ወደ ጣቢያ ወስደው ዋስ አስጠርተው  ተለቋል፡፡

አለማየሁ ለምን እንደታሰረ ሲጠይቅ “ለሊት የተበተነ ወረቀት ተጠርጥረህ ነው  “ጩኸታችን ይሰማ” የሚል የተጻፈ መፈክር አለ ይህንን ያለላንተ የሚሰራው የለም”  በማለት ነው ወስደውኝ የነበረው እና ግራ ገብቶኛል ሲል ገልጿል፡፡

 3/4 ኛው ሙስሊም የሆኑት የዶዶላ ፓሊሶች “ድምጻችን ይሰማ” የሚለውን ታዋቂ ድምጽ የየት የቱ እንደሆነ ሳያውቅ ወደ ቤተክርስቲያን ማተኮሩ ወደት ሊያመራ እንደሚችል መጠርጠር ይገባል ይላሉ በስፍራው ያነጋገርኩዋቸው፡፡

 

ከሻሸመኔ እስከ ማይጸብሪ

 

ከሻሸመኔ እስከ ማይጸብሪ  ቤተክርስቲያን ያለችበትን ሁኔታ ማወቅ ተስኗታል ይላሉ  አቶ ስራህብዙ ሲራክ (የህግ ባለሙያ)

               በሻሸመኔ ጥቅምት 29 ከ25 በላይ ለሆኑ የቤተክርስቲያን መሪዎች   ክርስቲያን ኮንሰርን በአዲስ አበባ ያዘጋጀውም ተመሳሳይ ስልጠና ያቀረበ ሲሆን፤  በቤተክርስያን ላይ እየተነሳ ያለውን መሰረታዊ ስደቶችን   እውነታ በእጃቸው ካለው ፍርድቤት ከሚያመላልሳቸው የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ጋር ያለውን በአካባቢው ያሉ  የህግ ባለሙያ አስረድተዋል፡፡ ከሻሸመኔ ከተማ ፤ ከሻሸመኔ ዙሪያ ከሃጄ ፤ ከአላባ፤ የተሰባሰቡ ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች  “ሰልጠናው የቤተክርስቲያን አይን ከፋች” ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

                በሻሸመኔ አንድ ፍርድ ቤት የተከናወነውን ለአብነት በማንሳት የችግሩን ግዝፈት የህግ ባለሙያው አቅርበዋል፡፡ ጉዳዩ     አንድ የቤተክርስቲያን ሰው የቤተክርስቲያን መስሪያ ቦታ ማጣትን  ችግርን አይተው መሬታቸውን ለቤተክርስቲያን ይሰጣሉ፡፡ በዘመናቸው ቤተክርስቲያንን አገልግለው በቤተክስቲያነ ጊቢ ይቀበራሉ፤  እንደ ኢትዮጵያ ክርስትና አስተሳሰብ፡፡ በቅርቡ ግን የተፈጠረው ክስ አባቴ የሞቱበት መሬት ላይ ክርስቲያን ሰው ሊቀበር ነው፤ መቀበር የለበትም!”  ብለው እንዳይቀበሩ የመሬቱ ባለቤትን እሬሳ ለሁለት ቀን ከቀብር አስተጓጉለዋል፡፡

ከልካዩ ሰው እንደምክንያት የሚያቀርቡት ይህ መሬት ለቤተክርስቲያን መሬት ከመሰጠቱ በፊት አባቴ ተቀብሮበታል የሚል ነው ፡፡ በፊት የሰውየው አባት እዛ መሬት ሲቀበሩ የመሬቱ ባለቤት ሙስሊም ነበሩ  አሁን ግን የመሬቱ ባለቤት  እምነታቸውን ቀይረወ ክርስቲያን ስለሆኑ አበቴ በተቀበረበት መሬት ላይ አሁን ክርስቲያን የሆነ ሰው መቀበር አይችልም!” ሲሉ በእምነት የሚመስሉአቸውን በማሰባሰብ እንዳይቀበሩ ይከለክላሉ፡፡  ከሁለት ቀን በሁዋላ የመሬቱ ባለቤት ለቤተክርስቲያን በሰጠት መሬት ላይ ተቀበሩ፡፡

    ተበዳይ ነኝ የሚሉት ሰውየው ግን ጉዳዩን ይዘው ወደ ፍርድ ቤት ይሄዳሉ፡፡  ክሱ ደግሞ አባቴ በተቀበሩበት ቦታ ላይ  ሌላ እምነት ያላቸው  መቀበሩን እቃወማለሁ” ከማለታቸው በተጨማሪ አባቴ ሌላ እምነት ያለው ስለሆነ እርሱ በተቀበረበት አካባቢ ቤተክርሰቲያን መስራት አይቻልም  በማለት ክስ የመሰረቱ  ሲሆን፤  ፍርድ ቤቱ ከነመጀመሪያው እንዲህ አይነት ክስ የማያስተናግዱበት መንገድ እያለ ዳኛው ግን የሟቹ እሬሳና ቀድሞ ተቀብሮአል ሲሉ የከሳሹ  ሰው አባት ያለው እርቀት እንዲለካ ትእዛዝ አስተላለፉ፡፡  ስለዚህ ከስድስት ሜትር ቅርበት ስላለው እሬሳው እንዲወጣ ቤተክርስቲያኑም እንዲፈርስ ጥያቄ ቀርቦ ተከሳሾሽ ክሱን እንዲከላከሉ ዳኛው ትዕዛዝ ያስተላልፋሉ፡፡

         እንደ አቶ ስራ ብዙ ገለጻ የመሬቱ ባለቤት በራሱ መሬት ላይ ተቀብሮ አያለ ፤  በአቅራቢያቸው ያለውን ፍርድ ቤቶቸ አሰራር በመተማመን የሚፈጥሩት ጫና ግን  ግራ አጋቢ ሲሆን፤ በመጨረሻም በተፈጠረው ክርክር ጉዳዩ ሊዘጋ ችሎአል፡፡  

   መሬት በህጋዊ መንገድ ቤተክርስቲያን ልታገኝ ባለመቻልዋ ከግለሰቦች በስጦታም ሆነ በግዢ  የተሰጡ መሬቶች በአዲሱ የመሬት ፓሊሲ  በጥቂት አመታት ውስጥ ለባለመሬቱ ሰለሚመለለስ መፍረስ የሚጠብቃቸው ብዙ ቤተክርስቲያኖች ናቸው ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ ይሁን እንጂ ሌሎች እምነቶች ግን በፈለጉት ቦታና ጊዜ በራሳቸው ፍላጎት ማምለኪያ ከሰሩ በሁዋላ ህጋዊ ለማድረግ ብዙ የማይከብዳቸው ሲሆን   ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች  ወንጀለኛ የሚያደርገው ህግ እነርሱን አለመንካቱ በቀጥታ አስደንጋጭ መሆኑን ተመልክተዋል፡፡

     ይህ ስልጠና የተሰጠበት አካባቢ በሃሰት በተቀነባበረ ክስ ብዙ ሰዎች እየታሰሩ እየተፈቱ የሚገኙ ሲሆን ለአብነት ያህል አለማየሁ ለገሰ የተሰኘ የመጽኃፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ተማሪ 3 ወራት ያህል ታስሮ ነበር ያለፍርድ፡፡ በዚህ ሰዓት ደግሞ ኦብሳ ኦገቶ የተባለ ሰው ሶስተኛ ወር እስራት ላይ ያለ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ከአስር ያላነሱ ክርስቲያኖች እየታሰሩ ተፈትዋል፡፡  ተሳታፊዎች ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ከፍተኛ የእምነት መብት ጥሰት እየተደረገብን ስለሆነ የሚከራከርልን ከጎናችን የሚቆምልን ያስፈልገናል፡፡ ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር መከራከር የህግ እውቀት የገንዘብ አቅብ የተቀነባበረ ጥቃትን የሚከላከል በወጥመድም ላለመውደቅ ከፍተኛ ትስስር የሚፈልግ እንደሆነ አይተናል ሲሉ ተሳታፊዎቸ ገልጸዋል

 ከስልጠናው መጨረሻ ላይ በየጊዜው በብዛት ለስደትነ ለእንግልት የሚዳረጉትን ክርስቲያኖች መልሶ ለማቋቋም የንብ አርባታ መስራት የሚቻልበትን እርሻ ለመየት ወንዶ ገነት የተጉዋዘን ሲሆን ምሺቱን ለኤርትራ ስደተኞችን ለመጎብኘት በአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በሰኣቱ ለመሄድ  ተጉዘን መቂ የተሰኘ ከተማ ላይ አዳር  አድርገን  ወደ  በረፋደ ላይ ወደ አክሱም ጉዞ አድርሰናል  ፡፡      

          የኤርትራ ክርስቲያን ስደተኞችን ለማየት ወደ ሽሬ ሄደን የነበረው ቢሆንም  ከስደትና ስደት ተመላሾች ቢሮ የተንዛዛ አሰራር  ከዚህ ሌላ የራስን ስራ ባግባብ ባለመስራት በተፈጠረ ቸግር ስደተኛ ካንፑን እንዳይመለከቱ ፍቃድ ስላልተሰጠን ወደ ስፍራው መግባት ተከልክለናል፡፡ የስደተኛው ሰፈር መግባት ማይ አይኔ ማይጸብሪ ሸማልባ እና የተባሉ ቦታዎች ከኢትዮ ኤርትራ ድንበር ሩቅ ስለነበር ሁለቱን አሜሪካዊያን ኤርትራዊ ይሆናሉ ብለው የሚያስጠረጥር ጉዳዮች አልነበሩም፡፡ ይሁን እንጂ የአሜሪካኖችን ፓስፖርትና ዶክመንቶች ካዩ በሁዋላ ወደ ካንፕ እንዳይሄዱ ተከልክለናል፡፡ 

በኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ባሉት ሸማልባ  ማይ አይኔ ና አደሃሪሽ ኀንጸት፡፡ ያሉ የተለያዪ የቤተክርስቲያን መሪዎች ስለአስከፊው ስደታቸው ያስረዱ ሲሆን የበለጠ አስከፊው ደግሞ በስደተኛ ካምፕ ውስጥም ሆነው የተባበሩት መንግስታት ስደተኛ ኮሚሺን መኪና የያዙ ኢትዮጵያዊ ባለስልጣናትም እምነትን መሰረት ያደረገ እንግልት የሚያደርጉ መሆኑን በአካል ያነጋገርናቸው ሰዎች መስክረውልናል፡፡ ስደት ና እንግልት የወንጌላዊያን ክርስቲያኖች እጣ ሆኖ መቀጠሉ አስገራሚ አድርጎታል፡፡  በመጨረሻም እንዳንሄድ እገዳ ባልተደረገበት አካባቢ የምንፈልጋቸው ስደተኞችን አግኘተን ቆይታ እንዳደረገን የኤርትራ ክርስቲያኖች አሁንም የአለም ህዝብን አትኩረት ስደት እንዲያበቃ ጥሪ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡ 

 

 

ሓረርከተማ“የሰማይብርሃን”ቤተክርስቲያንበአፍራሽግብረኃይልመፍረሱንየአይንእማኞችገለጡ

 

በእለቱ አፍራ ሾቹ ግዴታቸውን ጨርሰው ወደጁምአ ሄደዋልሲል የአይንእማኝ ለኢትዮክርስቲያን ገልጾአል፡፡ አፍራሹግብረሃይል እንደምክንያት የሚያቀርበው “ህጋዊፍቃድየላችሁም” የሚል ሲሆን እኛ ግን ለአምስት አመት የተጠቀምንበት ስለሆነና በቦታው ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ክርስቲያኖች የሚያመልኩበት በመሆኑ፤ልዋጭ ይሰጠን ወይም/ የፍርድቤት ትዕዛዝ ይሰጠን ስንል ብንለምናቸውም ሊሰሙን አልፈለጉም” ሲሉገልጸዋል፡፡ ከዚህ በባሰ መልኩ ቤታችን ሲፈርስ እንኳን ፎቶብናነሳ ከነሞባይላችን ለእስር ተወሰድን ሞባይላችን ተቀማ ሲሉገልጸው ፤ከየት እንደሆነ ያልታወቀ ስልክ ጥሪ እንደደረሳቸው ከሰዓታት በሁዋላ መፈታታቸውን ንብረታቸውም መመለሱንገልጸዋል፡፡

ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ላለፉተ 23  አመት ያህል ማምለኪያ ቤት መስሪያ ቦታ ማግኘት ህገመንግስታዊ መብታቸን ሆኖሳለ፤ የክልሉ መንግስት በማንአለብኝነት መብት ነፍጎ ሳይሠጥ የቆየ ሲሆን፤ አሁንም በግለሰብ ቤት ለጸሎት ስንሰበሰብ የሚፈርስበት ምክንያት የሃይማኖት ወገንተኝነት የሚመነጭ መሆኑን ማን ም ህጋዊ ተቋም ነኝ የሚልይ ህንን በደል ማስቆም ያለመቻሉ አሳፋሪነ ነው፤ይህም ሆን ተብሎ እኛ እንደምንበደል ይገባናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እውነታውም ቤቱን ለማፍረስ የቆየ እቅድ የተጠነሰሰ እንደሆነ ይገባናል የሚለው አንድክርስቲያን “  በመጀመሪያ አንድ እንግዳ ሰው ከማምለኪያ ቤቱ አጠገብ ያለን ቤት ቁልፍ ገዝተው ይገባሉ፤ ቀጥሎም ድምጽስ ለረበሸኝ ይህቤትይዘጋጅልኝ በማለትክስይጀምራሉ፤ ቀጥሎም እኚሁ ሰው በእሁድ አምልኮ ጊዜያችን ላይ ላሁአክባር በማለት ትልቅ ጎራዴ ይዘው ይገባሉ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከነጎራዴያቸው መግባታቸውን በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ ማቅረብ እንችላለንይላሉ …ይህን ለህግ አቅርበንም ሰሚ አላገኘንም፡: በሶስተኛደረጃደግሞ እንግዲህ ቀጣዩ ማፍረስ ሆነ ሲሉ ሃዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

መንግስት ያለ ፍርድቤት ትእዛዝ ይህ ማምለኪያ ቤት ማፍረስ ሲከናወን ከዚያማ ምለኪያ ቤት የሚያመልኩት 100 ክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆኑ በክርስትና አምነት አስተምህሮት ውስጥ ያሉ በየትም ቦታ ላይየሚገኙ ወንጌላዊያ ንክርስቲያኖች አካላዊ ህመም እንደሚፈጠር ያለመገመት ፈጽሞ ስህተት ነው በስልጣን ላይ ያለው ዢፓርቲና አጋር ድርጅቶቹ የዕምነትነጻነትን ህገመንግስታዊ መብትን ከማስከበር ይልቅ ሰፊ ቁጥር ካለው ህዝብ ለማስደሰት በመጣር ህግ ሲጣስ አላየሁም፥ አልሰማሁም፥የሚለው አቋምን ክርስቲያኖች ድምጻቸው ምንም ሊቀይር የሚችል አነስተኛ ግምት ከመገመት የሚወጣ እንደሆነ እንረዳለን ሲሉ ገልጸዋል ኢትዮክርስቲያን ያነጋገራቸው፡፡

አንዳንዶች ከዚህም ባለፈ “በመንግስትና በእስልምና እምነት መካከል ተከስቶ በነበረው ያለመግባባት ወንጌላዊያን ክርስቲያኖቸ እምነትን መሰረት ያደረገጥቃት በየቦታው ሲደርስባቸው ዝም በማለት መታረቂያ ስጦታ አድርጎ እንዳያቀርበን ስጋትአለን” ሲሉገልጸዋል፡፡

ኢትዮክርስቲያን ወንጌላዊያንክርስቲያኖችን በሻሸመኔ አካባቢ በስልጢ በሃረሪ ክልላዊመንግስት ስር እንዲሁም እዚሁአዲስአበባ ውስጥ ፤ በመጀመሪያ ማምለኪያ በታ መከልከል ቀጥሎም በኪራይ ቤት ማምለክ አትችሉም የሚል ማስታወቂያ በመንገር ማሰርና ማንገላታት እነደፋሺን የተያዘ የታቀደ የተደራጀ በመዋቅር የሚሰራ እምነት መሰረት ያደረገ ጥቃት መቆምአለበት ብለን እናምናለን፡፡እውነታው ግን መሬትየህዝብና የመንግስት ነው እያለ የሚናገር መንግስት የእምነት ማካሄጃ ቦታ ስጦ  መንግስት  ህገመንግስታዊ ግዴታ   መወጣትይኖርበታል፡፡

 

 

 

 

 

ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን ለመጀመሪያ ጊዜ ስደትና ምከንያቶቻቸውን ከሚመለከታቸው ባለጉዳዮች ጋር በአዲስ አበባ ምክክርና ስልጠና አደረገ

 

 

ከሌሎች እምነት ጋር ሲነጻጸር ወንጌላውያን ክርስቲያኖች በቁጥር አነስተኛ በሆኑባቸው አካባቢዎች፥ የሚደርስባቸውን እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት ምክንያት ምንነት እና የመፍትሄዎችን ፤  ከሃገሪቱ ህገመንግስት፥ ከመጽኃፍ ቅዱስ አስተምህሮትና አለማቀፋዊና ሃገራዊ እይታዎች ጋር በማጣመር የምክክር ጊዜ በጥቅምት 18 ቀን በአደስ አበባ ተደርጎ ነበር፡፡

የምክክር ጊዜው የተዘጋጀው በኢንተርናሽናል ክርስቲን ኮንሰርን እንደመሆኑ መጠን ጉዳዩን ለማመቻቸት ከዋሽንግትን ዲሲ  ዊሊያም ስትሮክ እና ካሜሩን ተማስ የተሰኙ የኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን የኢዥያ ሃላፊና የአፍሪካ ዳይሬክተሮች በቦታው ተገኝተው ነበር፡፡

የምክክር ጊዜው ዋና ሃሳብ “በኢትዮጵያ ውስጥ የለውን እምነትን መሰረት ያደረገ ጥቃት እንዴት ማስወገድ ይቻላል?” ለሚል ጥያቄ መለስ መስጠትን ያለመ ነው፡፡  መጽሃፍ ቅዱስንና የቤተክርስቲያን ተሞክሮን፤ የኢትየጵያ ህጎችን ከአለማቀፍ ህጎች ጋር አንድነት ያለው  በማጣመር የጉዳቱ ተጠቂ የሆኑትን ወንጌላዊያን ክርስቲያኖችን የአሁኑን ችግሮች ቃኝቷቸዋል፡፡

 ኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርን በአለማቀፉ የክርስቶስ አካል ያለውን የግንኙነት ክፍተት ለመሙላት የተቋቋመ በመሆኑ  በኢትዮጵያ ውስጥ ስደት የለም ብለው የሚያስቡትን የምዕራቡ ዓለም ቤተክርስቲያናትና እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖሩ አብዛኛው የቤተክርስቲያኖች መሪዎችን  ለማሳሰብና በኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደ ችግር አለ ብሎ የሚቀርበውን ሃሳብ እንደ አንድ የክረስቶስ አካል የአንዱ ጉዳት የሌላውም ጉዳት መሆኑን ለማሳየት የተዘጋጀ እቅድም ነበር፤  እንድ አፍሪካ ዳይሬክተር ካሜሩን ቶማስ ገለጻ ፡፡

በስልጠናው ላይ ተናጋሪዎች ስልጠናውን በተሞክሮም በታሪክም በማስረጃም በማጣቀስ ንግግር ሊያደርጉ የቀረቡት ሁሉ በአንድነት መጠነ ሰፊ የመብት ጥሰት እንደሚደረግ የሚያውቁ ሆነው ጉዳቱን ለመቀነስ የሚደረገውን መንገድ ግን በራሳቸው አተያየይ  ሆኖ የተለያየ ማብራሪያ ቀርቦበታል፡፡

በኢትዮጵያ ድህረ ምረቃ ስነመለኮት ኮሌጅ ላይ የቀረበው የመጀመሪያው መክፈቻ ንግግር በመብትን መተውና በመስዋዕትነት መካከል ያለው ልዩነት “ስደት ወይሰ ሰማዕትነት”  በሚል የቀረበው ጽሁፍ ፤ ክርስትና በደምና በመስዋዕትነት ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሸጋገረ  እምነት ሆኖም ቀጥሎአል ሲሉ ፤ በዚህ የእምነት ነጻነት ባለበት ዘመንም ይህንን መስዋዕትነት እየከፈልን መሄዳችንን ይፈለግብን ይሆን ወይ ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይፈለግብናል ከተባለ ቤተከርስቲያን የመስዋዕተነት መዝሙሮችን ስብከቶችን  አሁንም መስበክ ይኖርባት ነበር፤ ካልሆነ የማያስፈልግ ነው ህግና ስርዓት ይመራናል ካለች ደግሞ በደሎችን ለማስቀረት የምትሰራው ስራ የታለ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ወታደራዊው ደርግ ቤተክርስቲያን ላይ በግልጽ  በአዋጅ ወይም ያለአወጅ ጥቃት ሲዘነዘር  በወታደራዊ ማርሽ በተሰራው “ድሉ የጌታችን ነው ድሉ የአምላካችን ነው ድሉ” በማለተ በስብከትና በዝማሬ ከመከራው ጋር የተሟገቱ መሪዎችና ተከታዮች የነበራቸው ሲሆን ፤ አሁን አምሮብናል በቤትህ የሚል ዜማ እያዜምን ” እህቶቻችንና ወንድሞቻችን ለጉዳት አሳልፈን ሰጥተን ተቀምጠናል ..ሰላም ነው እንላለን ሰላም ከሆነ እሺ ሰለሙ የሚያጡት ከየት መጡ ተሰዳጆች ከየት ወጡ .ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላኛው ተናጋሪ ወንጌላዊያንን ክርስቲያኖች ጥያቄ አለኝ ሲሉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ለሁለት ሺ ዘመን ሰላሙዋንና ሃገርን ጠብቃ የቆየችበትን መንገድ የገለጹ ሲሆን  ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ገና ብዙ ያልሰሩት የቤት ስራ እንዳላቸው ማሳሰቢያዎቸን አቅርበዋል፡፡ አያይዘውም ፤ ወንጌላዊያን ቤተክርስቲያን አማኞች ቤታቸው ሲቃጠል፤ ቤተክርስቲያን ሲቃጠል፤  እህቶቻቸው ተነጠቀው ቢደፈሩ ያላቸው ምላሾች “ጌታ ይቅር ይበልህ ጌታ ይወድሃል” የሚል እስከሆነ ድረስ …ሊያጠቃቸው የሚመጣውም ቢሆን ጌታዬ ይወደኛል ይህንን ባደርግ ብሎ ሀገመንግሰትም ሆነ መጽሓፍ ቅዱስን ተቃርኖ የሚመጣም ቢሆን ..ጌታው እንደሚወደው ማረጋገጫ ከወንጌላዊያን እንደሚሰጠው የታወቀ  ስለሆነ ፤ ችግሩን የማቆመም አዝማሚያም እንደማይኖረው ለጊዜው የሚታይ ፍንጭ እንደሌለ ፤ ይልቁንም ለነገ ምን ቢደረግ እንደሚገባ  ቁጭ ብሎ የማሰብ ልማድ እስከሚያውቁት ድረስ እንደሌለ ጠርጥረዋል፡፡ መጽሓፍ ቅዱስ ላይ  ግን እንደ ክርስቶስ አካል ከፊት ለፊቱ ያለውን ባታሊዎን ለመገመት ቁጭ ብሎ ሂሳብ የማይሰራ ማን ነው ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ለሁለቱም የመጀመሪያው ዙር ስልጠና አቅራቢዎች ከተሳታፊዎች “ሰላም አለ  ከመንግስት ጋር እየሰራን ነው” የሚሉ የወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ጽ/ቤት ተወካዩች ሃሳባቸውን የገለጹ ሲሆን እስካሁን የተሰራውንም ማመስገን ይኖርበናል፡  ሙሉ በሙሉ ችግር አለማለት አይቻልም ሲሉ ምክር ለግሰዋል፡፡ 

በምላሹ የሰላም ትርጉም፤ የፍቅር ትርጉም አሻሚነት ለውይይት ቀርቦአል፡፡ ፍቅር ያፈቅራል እንጂ አይቆጣም  የሚል አሳብና የማይቆጣ ፍቅር አምላካዊ አይደለም  ሰው ስለፍቅር ሁሉን ቢሰጥ ፈጽሞ እንደሚናቅ የሚያስረዱ አስረጂዎች የተሳታፊውን አእምሮ ይዞ ነበር፡፡

ወንጌላዊያን ችግሮቻቸው መጽኃፍ ችግር ፈቺ ስነመለከኮት የሌላቸው መሆኑ አንዱ የችግሩ ምንጭ እንደሆነ ያቀረቡት ሁለተኛ ተናጋሪ ያልተመለሱ መጽሃፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችንም አንስተዋል፡፡ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ያኛውንም ጉንጭህን ደግሞ አዙርለት የሚለውን አስተምህሮ ቃል በቃል በተግባር ለማዋል ለሚታገሉ ወንጌላዊያን ክርስቲያኖች  ማን ይድረስላቸው ይሆን  የሚል አስተያየት አዘል አቅርበው ወንጌላዊያን ክርስቲያኖቸን ሞግተዋል፡፡ በማያያዝም ይህንን ቃለ ኢየሱስ ወይም ሃዋሪያው ጳውሎስ እንዴት በተግባር  እንደመለሰው ዘለው ያነባሉ ያሉት ቄስ ..ኢየሱስ በጥፊ ሲመታ ለምን ትመታኛለህ ማለቱን ፤ ሓዋሪያው ጳውሎስ አንተ በኖራ የተለሰንክ ግድግዳ ብሎ መመለሱን  በሸንጎ ሲፈረድበት ይግባኝ መጠየቁንና ሁሉንም እጁን አጣጥፎ ያለመጠበቁን ይልቁንም እምነትን ለመጠበቅ ያሉትን ሁሉንም እድሎች አሙዋጦ መጠቀምን  የሚነግረውን መጽሐፍ ቅዱስ ከሃዋሪያው በላይ መንፈሳዊ ለመሆን ለወንጌላዊያን ክርስቲያኖች ምን እንዳነሳሳቸው  ለማወቅ እንደሚፈልጉ  በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ከምግብ እረፍት ቀጥሎ ተሳታፊዎች ከሃረር ሓረሪ ክልላዊ መንግስት ስር የሚደርስባቸውን እምነትን መሰረት ያደረገ ትንኮሳ የመብት ጥሰት በዝርዝር አንስተዋል፤ በስልጢ ዞን የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ለማዘጋት ለሰባት አመታት የፈጀን  በመንግስት ባጀት ቤተክርስቲያንን ለመዝጋት  የሚደረግን ክርርክር አስታውሶ የቤተክርስቲያን አቅም ውስንነት  ሁኔታውን ምን ያህል ፈታኝ አድርጎት እንደነበር የቤተክርስቲያን መሪዎች ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡ በዚሁ ቦታ  ቤታቸው በመጋዝ ተቆርጦ የተጣለባቸው ከደደር ቁፋንዚክ የመጡት አቶ ፍቅሬ መንግስቱ የገጠማቸውን፤  ለህግ ባለሙያዎች ያልተፈተሸ መንገድ የለም በማለት የሁኔታውን አስቸጋሪነት አቅርበዋል፡፡ እንዲሁም አንድ ሴት ተሳታፊ በፍርድ ቤት ደጃች በዱላ መደብደባቸውን ጉዳዩን ዳኞች ገዋናቸውን እንደለበሱ ያየበትን መስክረው ከተደበደቡበት ክልል እስካሁንም ድረስ ህግ ፊት ያለመቅረባቸውን ለተሳታፊው አቅርበዋል፡፡

በሶስተኛ ክፍለጊዜ የቀረበው የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ተሳታፊዎች የደረሰባቸውን ችግሮች ከሰሙ በሁዋላ የቀረበ ስለነበር ያሉት ችግሮች እንዳሉ ሆነው ችግሮቹ አሁን የያዙትን መልክ የያዙት ቤተክርስቲያን ማድረግ የሚገባትን ስላላደረገች ነው በማለት ለአብነት ያህል አስረድተዋል፡፡ በግለሰብ ደረጃ ከሚደርሰው ጥቃት ጀምሮ የማምለኪያ ቤት መስሪያ ቦታ ተየይዞ የሚነሱ ችግሮችን ቤተክርስቲያን ሃላፊነት ወስዳ ልትሰራው የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ህገመንግስታዊ ውክልናም ሆነ ተቀባይነት እያለ በስርዋ የተጠለሉትን ህዝቦችዋን እንዴት ያለ እረኛ እንዳስቀረች አስረድተዋል፡፡  ቤተክርስቲያን በውስጡዋ በህግ ባለሙያዎች የተከበበች ሆና እያለ የምትስራቸውን ስራዎች ህግ ሊፈቅደው በሚችል መልኩ መስራት ባለመቻልዋ፤ በቀላል ተለማማጅ የህግ አማካሪ ሊፈቱ የሚችለሉ የአካሄድ እርምጃዎችን ባለማማክርዋ ለጉዳት ተላልፋ ተስጥታለች፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ የአምልኮ ቦታ ማግኘት ህገመንግስታዊ መብት ሆኖ እያለ የሃገሪቱ የመሬት ህግ ምን እንደሚመስል ሳታውቅ በነጻ ልታገኝ የሚገባትን መሬት ከግለሰቦች በመግዛት ወዲያውም ደግሞ በመመሳጠር የመሬት ህጉን ባለማወቅ በሚሰራ ክፍተት እንዴት መልሶ ለመፍረስ እንደምትዳረግ የህዝቦችዋን ሃብትና ንብረት ሞራልም ሆነ ተስፋ እንዲዝረከረክ እንዳደረገች ከተሞክሮአቸውም ሆነ ከያዙት አያሌ የህግ ጉዳዮች ዋቢ በማድረግ ገልጸዋል፡፡

የቱንም ያህል ከባድ ቢሆኑም ፍርድቤቶችን ሰብዓዊ መብት ኮሚሺንንና የእንባ ጠባቂ ተቁዋማትን በመጠቀም በቤተክርስቲያን ላይ የሚነሳውን ከህግ ውጪ የሚደረግን ጥቃት ማስቆም እንደሚገባ አበክረው የገለጹ ቢሆንም  እንደሃረሪ ክልል ስልጤ አካባቢ ከሻሸመኔ አካባቢ የመጡ ተሳታፊዎች ግን ሁሉም ተሞክረው የከሸፉ የህግ የበላይነትን ማስፈጸም የተሳናቸው ተቁዋማትን እንደመፍትሄ ማቅረብ እንደማያዋጣ ..ይልቅ ድምጻችንን  እንዲሰማ የሚሰማውን ሰሚ  አካልን የመፍጠር ስራ እንዲሰራ አበክረው ተናግረዋል፡፡   ጥንካራ ምላሽ የገጠማቸው  የህግ ባለሙያም የሚወጡ አፋኝ ህጎችም ሆነ የቤተክርስቲያንን ጥሪ የማያኮስስ ከህገመንግስቱ ውጪ የሚደረጉ ግፊቶቸን ህገመንግስታዊ መብቶችን በመጠቀም ቤተክርስቲያን ለህግና ህግ መከበር በመስራት ያሉትን እድሎች እስከሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት በደሎች እንዲቆሙ ድምጻችንን ማሰማት የሚገባ መሆኑን ይህም ህግ የሚፈቅደው አካሄድ መሆኑን የህግ ባለሙያዮዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡

በመጨረሻም  ህጋዊ ድጋፍ በሚፈልጉ ጊዜ አቅም አልባ ለሆኑ የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ድጋፍ እንደሚያደርግ ቤተክርስቲያንን በመብትና ግዴታ ዙሪያ የምክር ስልጠና እንደሚሰጡ በሃገሪቱ ውስጥ ቢሮዎችን በማስፋፋት ህጋዊና ህጋዊነት እንዲሰፍን አጥብቀው እንደሚሰሩ የገለጹ ሲሆን 16 ሚሊዮን ወንጌላዊያን ጥያቄዎችን መዝለል የሚፈለግ ኢትዮጵያዊ ተቁዋም ሊኖር አይችልም ቸል ካማለት የሚመጡ ብሆኑ ነው እንጂ ፤ ችግሮቹ ተነጋግሮና ተፈላልጎ መስመሮችን ማስተካክል ነው የሚጠበቀው ሲሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል፡፡

በማጠቃለያም የኢንተርናሽናል ክርስቲያን ኮንሰርነን ተወካዮች በኢትዮጵያም ሆነ በአፍሪካ ውስጥ የሚሰሙትን እምነትን መሰረት ያደረገ ተጸእኖ አለም እንዲያውቀው በማድረግ የሚመለከታቸው ሰዎች ምላሻቻን  እንዲሰጡ በአለማቀፍ ደረጃ አለማቀፍ በሆኑ ተቁዋማት በኩል እንዲሁም በግለሰብ ደረጃ በየትኛውም የአገር አንዲት አጥቢያም ቢሆን በህግና በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ከቤተክርስቲያን ጋር በመሆን ህጋዊ ባለሙያዎችን በመጠቀም ችግሮች ማሳወቅ መከላከል ድጋፍ ማድረግ እንዲሚደረግ አስታውቀው፤  ከሁሉ በላይ የአንዲት አላማቀፋዊትዋ ቤተክርስቲያን አካል የሆነ ሁሉ የአንዱ ጉዳት የሁሉ ጉዳት መሆኑን በማሳወቅ እንሰራለን ብለዋል ዊሊያም  ስታርክና  እና ካሜሩን ቶማስ፡፡ 

Facebook Like Button

Digi-Komp Google +1 Slider